ቀጥታ፡

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ከዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19/2018 (ኢዜአ)፦ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ከዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚቻል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸውን የድረ-ገጽ፣ የቴሌግራምና አጭር የጽሑፍ መልዕክት አድራሻዎችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ከምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎች (Link) በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-

📌በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et

📌ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram

📌አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም