የመውሊድን በዓል አንድነትንና መደጋገፍን በሚያጠናክር መልኩ ማክበር ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
የመውሊድን በዓል አንድነትንና መደጋገፍን በሚያጠናክር መልኩ ማክበር ይገባል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19/2018 (ኢዜአ)፦ የመውሊድን በዓል አንድነትንና መረዳዳትን በሚያጠናክር መልኩ ማክበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስገነዘበ።
የዘንድሮው 1ሺህ 501ኛ የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የመውሊድን በዓል የአንድነትንና መረዳዳትን በሚያጠናክር መልኩ ማክበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዓሉን ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ወገኖች ጋር አብሮ ማክበር እንደሚገባም ገልጸዋል።
ሼህ አብዱልከሪም ዘለቂ ሰላምን፣ ልማትንና አንድነትን ለማስጠበቅ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ መሐመድ ሸሪፍ በበኩላቸው፣ የመውሊድ በዓል የነብዩ መሀመድን አርአያነት በተግባር በማሳየት ማክበር ይገባል ብለዋል።