ቼልሲ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ቼልሲ ፉልሃምን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ማምሻውን በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ፣ ሞርጋን ሮጀርስ እና ኮል ፓልመር የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ጆአኦ ፔድሮ በ31ኛው ሴኮንድ ያስቆጠረው የዓመቱ ፈጣን ጎል ሆኖ ተመዝግቧል።
ጆሹዋ ኪንግ እና ጎንዛሎ ጋርሺያ የፉልሃምን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ከአስቶንቪላ ወደ
ቼልሲ የተዘዋወረው ሞርጋን ሮጀርስ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታው ጎል አስቆጥሯል።
ከሪያል ማድሪድ ፉልሃምን የተቀላቀለው ጎንዛሎ ጋርሺያም የመጀመሪያ የሊግ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ጨዋታው እጅግ አዝናኝና በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት ነበር።
የቼልሲው አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ በመጀመሪያ ጨዋታው ድል ቀንቶታል።
በአንጻሩ አዲሱ የፉልሃም አዲሱ አሰልጣኝ አርቫሎ አርቤሎአ በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግዷል።
ጨዋታውን ተከትሎ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።
የሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ከአርብ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።