ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ ለካፍ አስገባች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ ለካፍ አስገባች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ (Bid Document) ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስገብታለች።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ዶክመንቶችን ያካተተ ሰነድ (BID HAND BOOK) ለካፍ ማስገባቱን አመልክቷል።
ይህም ኢትዮጵያ ታላቅ አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለአራተኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ ዝግጁነቷን ማረጋገጧን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።