ኒውካስትል ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኒውካስትል ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶኒ ኢላንጋ እና ጆ ዊሎክ ለኒውካስትል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኮዲ ጋፕኮ እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ለሊቨርፑል ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ስቦዝላይ በ99ኛ ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ጎል ሊቨርፑልን አቻ አድርጓል።
ኒውካስትል በማትያስ ጃይልስ፣ ሊቨርፑል በአንዶኒ ኢራኦላ በመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ነጥብ አሳክተዋል።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1፣ ብራይተን አስቶንቪላን 4 ለ 0 አሸንፈዋል።