ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርከስ ታቫርኒየር በ26ኛው ደቂቃ የየቦርንማውዝ የመሪነትን ጎል አስቆጥሯል።

የሲቲ ተከላካይ መስመር ድክመት ለግቡ መቆጠር ምክንያት ሆኗል።

ማርክ ጌሂ በ84ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ሲቲ አቻ ሆኗል።

ጆሽኮ ግቫርዲዮል በ92ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጓል።

ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ በጨዋታው ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

አዲሱ የሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ድል ቀንቷቸዋል።

በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ብራይተን አስቶንቪላን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

ጃክ ሂንሺልውድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ማክሲም ዲ ካይፐር እና የአስቶንቪላው ቪክቶር ሊንድሎፍ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የአስቶንቪላው ጆአኦ ጎሜዝ በ40ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ወጥቷል።

የወቅቱ የዩሮፓ ሊግ አስቶንቪላ አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በ10 ተጫዋች መጫወቱ ለብራይተን ከፍተኛ ብልጫ መውሰድ ምክንያት ሆኗል።

ከደቂቃዎች በኋላ 12 ሰዓት ከ30 ላይ ኒውካስትል ዩናይትድ ከሊቨርፑል በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም