ቀጥታ፡

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ሪከርድን ሰበረ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/ 2018 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቦነስ አይረስ በተካሄደው ውድድር የግማሽ ማራቶን ሪከርድ ሰብሯል።

የሩጫ ታሪክን እየፃፈ የሚገኘው አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን በ56 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በማጠናቀቅ አዲስ የዓለም ሪከርድ አስመዝግቧል።

በዚህም አትሌት ዮሚፍ ዩጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ ከዚህ በፊት አስመዝግቦት የነበረውን 57 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ የዓለም ሪከርድ በ29 ሴከንዶች በማሻሻል የርቀቱ የዓለም ፈጣን አትሌት መሆኑን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም