ብሬትንፎርድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸንፏል - ኢዜአ አማርኛ
ብሬትንፎርድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸንፏል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 0 ረትቷል።
ማምሻውን በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪን ሉዊስ-ፖተር፣ ቫይታሊ ጃኔሌት እና ማይክል ካዮዴ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢጎር ቲያጎ በ55ኛው ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል።
ባለሜዳው ብሬንትፎርድ ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን ወደ ግብ በመቀየር ውጤታማ ነበር።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በጨዋታው ላይ ደካማ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ግልጽ የግብ እድሎችን መፍጠር ተስኖታል።
ብሬንትፎርድ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ጀምሯል።
በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ገንዘብ ያፈሰሰው ቶተንሃም በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል።