ኤቨርተን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ኤፕስዊች ታውን ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
ኤቨርተን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ኤፕስዊች ታውን ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።
ማምሻውን በሂል ዲክንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 ረትቷል።
ኪርናን ዴውስበሪ-ሆል እና ቲዬርኖ ባሪ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ባለፈው የውድድር ዓመት 13ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኤቨርተን በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ድል ቀንቶታል።
ተጋጣሚው ክሪስታል ፓላስ ዓመቱን በሽንፈት ጀምሯል።
በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 አሸንፏል።
አንቶን ስታች የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በፖርትማን ሮድ በተካሄደው ጨዋታ አዲስ አዳጊው ኤፕስዊች ታውን ሰንደርላንድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ኤመርሰን እና ጃክ ክላርክ ለኤፕስዊች ግቦቹን አስቆጥረዋል። ኒልሰን አንጉሎ ለሰንደርላንድ ጎሏን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቀን ላይ በተደረገ መርሐ ግብር አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።