ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ በአዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ሽንፈት አስተናገደ 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሁል ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በኤምኬኤም ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴሚ አጃይ እና ኖቤል ሜንዲ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ባለሜዳው ሁል ሲቲ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱንም ግቦች አስቆጥሯል። ቡድኑ ውጤቱን አስጠብቆ ወጥቷል።

ማንችስተር ዩናይትድ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ወደ ጨዋታው ለመመለስ የሚያስችሉትን ግቦች ማስቆጠር አልቻለም።

ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ወደ ሊጉ የተመለሰው ሁል ሲቲ ሳይጠበቅ ወሳኝ ድል አሳክቷል።

ሁል ሲቲ በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩናይትድን አሸንፏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም