ቀጥታ፡

ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የመላው ኢትዮጵያውያን እውነተኛ መድረክ በሆነ መልኩ ተከናውኗል - ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ መካሄዱ የመላው ኢትዮጵያውያን እውነተኛ መድረክ እንዳደረገው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ስነ ስርዓት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በኢትዮጵያ የፖለቲካና ማህበራዊ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው።

ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶችን በሃይል ለመፍታት ከመሞከር እና ከመገፋፋት ይልቅ በመነጋገር፣ በመደማመጥ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን በጉባኤው ላይ ማሳየታቸውን አስታውቀዋል።

በመሰረታዊ አለመግባባቶች እና የሀሳብ ልዩነቶችን በንግግር ለመፍታት የታየው ጥረት አዲስ የፖለቲካ ባህልን የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉባኤው አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ መከናወኑንና ይህም የመላው ኢትዮጵያውያን እውነተኛ መድረክ እንዲሆን ማድረጉን አመልክተዋል።

በጉባኤው ላይ በስምንት አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ጠቅሰው የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም ዋናው ትኩረት ኢትዮጵያን ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ለነገዋ ኢትዮጵያ መጻኢ ጊዜ ጠንካራ መሰረትን የሚጥል ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም