ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የኢጋድ ዋና ጸኃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ፣ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የተሳካ ምክክር በማካሄድ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ነው።

በምክክሩ አጠቃላይ ሂደትም ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ለመላ አፍሪካዊያን ምሳሌ የሚሆን ስራ አከናውናበታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም