ቀጥታ፡

ሻምፒዮኑ አርሰናል የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን በድል ጀምሯል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ መርሐ ግብር አርሰናል ኮቨንተሪ ሲቲን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ካይ ሃቫርትዝ፣ ቡካዮ ሳካ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሃቫርትዝ በ15ኛው ደቂቃ የአዲሱን የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የኮቨንተሪው ካሌብ ይሬንቺ በ27ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።

አርሰናል በጨዋታው ከፍተኛ ብልጫ ወስዷል።

አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ የግብ እድሎችን መፍጠር ተስኖታል።

ሻምፒዮኑ አርሰናል የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን በድል ጀምሯል።

አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በመጀመሪያው ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል።

የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም