ቀጥታ፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በዚህ መሠረት፦

1- የማህበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ተጠቃሚዎች መዋጮን ለማሻሻል የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

2- ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች (ለሆቴል፣ ለሞልና አፓርትመንት፣ ኢንዱስትሪ፣ ለበጎ አድራጎት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና የህክምና ተቋማት) የማስፋፍያና አዳዲስ የመሬት ጥያቄዎችን ለመመለስ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አፅድቋል።

3- በከፊል በኮሪደር ለምተው፣ በከፊል ሳይለሙ የቆዩ አካባቦዎችን በተሟላ ሁኔታ ለማልማት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።


 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም