ቀጥታ፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤ ተግባራዊ መገለጫ ነው

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤ ተግባራዊ መገለጫ መሆኑን የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትና ኢኒሼቲቮችን አፈፃፀም ገምግሟል።

በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት፥ በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።

በተለይ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ- ግብር የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱና ተጠቃሚነትን ለሚያረጋግጡ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዚህም የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና መልሶ ግንባታ፣የአካባቢ ንጽህና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትና የትምህርት ቁሳ ቁስ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራዎች መጠናከራቸውን ቀጥለዋል።

የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤ ማሳያ ነው ያሉት ሀላፊው፥ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም