ቀጥታ፡

በዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ዙሪያ ከዩናይትድ ኪንግደም የድርድር ቡድን ጋር ውይይት እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 12/2018 (ኢዜአ)፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዩናይትድ ኪንግደም የድርድር ቡድን ጋር የሚያካሂደው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በመክፈቻው ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) 23 ዓመታት በላይ የወሰደውን የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር 2026 መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለዩናይትድ ኪንግደም የድርድር ኮሚቴ አባላት አብራርተዋል።


 

ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የልማት ፍላጎቷን ያገናዘበ ገንቢና መፍትሔ-ተኮር የገበያ ሁኔታ ማቅረቧን እና እስከ አሁን 11 ሀገራት ጋር ድርድር ማጠናቀቋን አረጋግጠዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ለሚያደርገው ድጋፍና አጋርነት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት ስምምነቱን በይፋ ለመፈራረም የሚያስችል ውጤት እንደሚጠበቅም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም