የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
ጋምቤላ፤ ነሀሴ 12/2018 (ኢዜአ)፡- የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ኡማን አሙሉ (ዶ/ር) የክልሉን የ2019 ረቂቅ በጀት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የክልሉ የ2019 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ ማስፈፀሚያ 18 ቢሊዮን 577 ሚሊዮን 523 ሺህ 685 ብር ረቂቅ በጀት መሆኑን ለጉባኤው በዝርዝር አቅርበዋል ።
በጀቱ ከክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢና ከፌዴራል መንግስት የሚሸፈን መሆኑን አመልክተዋል ።
ምክር ቤቱ በረቂቅ በጀቱ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል ።