ቀጥታ፡

13ኛው የጤና ፌዴሬሽኖች ኮንፍረንስ እና ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 12/2018 (ኢዜአ)፦13ኛው የጤና ፌዴሬሽኖች ኮንፍረንስ እና ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ከነሐሴ 15 እስከ 17 ቀን 2018 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዓለም አቀፍ ሁነት በማስመልከት የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ፌዴሬሽን በጋራ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በኮንፍረንሱ እና ዓለም አቀፍን ኤግዚቢሽኑ ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ 2 ሺህ መሪዎችን፣ ባለሙያዎችንና ተመራማሪዎች እንዲሁም ከ30 በላይ የሚሆኑ ከሀገር ውስጥና የውጭ አቅራቢዎች እንደሚሳተፉም ተጠቁሟል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ በመግለጫቸው እንዳሉት ጉባኤው መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን በሀገር ውስጥና በቀጣናው በማምረት ከውጭ የሚመጡ ምርቶች ላይ ያለን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ለጤናው ዘርፍ የሚውል የግል ካፒታል ማሰባሰብና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን መዘርጋት ላይም እንዲሁ።

በተጨማሪም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስር የጤና ንግድ ሰንሰለቶችን እና የጋራ ገበያዎችን ለማጠናከር የፖሊሲ ውይይቶችና የንግድ ስምምነቶች እንደሚደረጉ ጨምረው ገልጸዋል።

በጉባኤው የምስራቅ አፍሪካ የጤና ኢኮኖሚን መገንባት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ እና ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን የተመለከቱ የጎንዮሽ ውይይቶች እንደሚደረጉም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም