ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አድርገው ሾመዋል።
በሌላ በኩል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።