የአፋር ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአፋር ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ አፀደቀ
ሰመራ ፤ ነሐሴ 4/2018(ኢዜአ) ፦ የአፋር ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።
ምክር ቤቱ ነሐሴ 2ቀን 2019 ዓ.ም የጀመረው 6ኛ የምርጫ ዘመን፣ 5ኛ የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን በሰመራ ከተማ ማካሄዱን ቀጥሏል።
በጉባዔው ተገኝተው የክልሉን የ2019 ረቂቅ በጀት ያቀረቡት የገንዘብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረሳ መሐመድ እንዳሉት፤ በጀቱ ከመንግሥት ድጎማ ከክልሉ የውስጥ ገቢ፣ ከፌዴራልና ከተለያዩ ሌሎች አማራጮች የሚሸፈን ነው።
ለበጀት ዓመቱ የተመደበው ገንዘብ የክልሉን ልማት ለማቀላጠፍና የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑንም አመላክተዋል።
ምክር ቤቱ ከበጀቱ በተጨማሪ ሁለት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ያፀደቀ ሲሆን፤ ቀጥሎም የዳኞችን ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።