ምክር ቤቱ በህዝብ የተሰጠውን አደራ በመወጣት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በየደረጃው አሳድጓል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ በህዝብ የተሰጠውን አደራ በመወጣት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በየደረጃው አሳድጓል
ሰመራ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ) ፦ምክር ቤቱ በህዝብ የተሰጠውን አደራ በመወጣት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በየደረጃው ማሳደግ መቻሉን የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሲያ ከማል ገለጹ።
የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣5ኛ የስራ ዘመን፣10ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሔድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚያካሔደው ጉባኤ የክልሉን አስፈፃሚ አካላት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲተር የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ያደርጋል።
ጉባዔውን ያስጀመሩት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሲያ ከማል እንዳሉት፤ ምክር ቤቱ በህዝብ የተሰጠውን አደራ በመወጣት የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ተግባራት አከናውኗል።
በዚህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማደጉን ነው የገለጹት።