ቀጥታ፡

የአፋር ክልል ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ መደበኛ ጉባዔውን ያካሂዳል

ሰመራ፤ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የአፋር ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሲያ ከማል ገለጹ።

አፈ ጉባዔ አሲያ ከማል በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምክር ቤቱ በሚኖረው ቆይታ የክልሉን ስራ አስፈፃሚ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዲተር የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚያደረግ ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛው ጉባዔ የተለያዩ አዋጆችን እንደሚያፀድቅም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም