ቀጥታ፡

ብሔራዊ ባንክ ለማህበረሰቡ ልማት መጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል-ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፦ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት ለማህበረሰቡ ልማት መጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለፁ።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዊ ዞን ለተጋላጭ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት መሠረት በመጣል፣ የትምህርት እቃዎችን በማከፋፈል እና በዛፍ ተከላ ኘሮግራም ላይ በመሳተፍ ለማህበረሰቡ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል ነው ያሉት።


 

እነዚህ ስራዋች የባንኩ ለብሔራዊ ልማት፣ለአካባቢ ዘላቂነት እና በመላ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ክፍሎችን ለመገንባት የሚሰራውን ስራ የሚያሳይ ቀጣይ ድጋፍ ነው ብለዋል።

በየትኛውም አካባቢ የምንኖር ኢትዮጵያውያን እጅግ ተቆራኝተን በአንድነት የምንኖር፣ሕዝቦች ነን ያሉት የባንኩ ገዥ፣ ይህም አንድነታችን ማንም ሊከፋፍለው የማይችል ነው ሲሉም  ተናግረዋል።

አያይዘውም ”የአዊ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያዊ አንድነቱን አስጠብቆ የኖረ፣ የጥንካሬ ምልክት የሆነ ሕዝብ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም