ቀጥታ፡

 ሰላምና ፀጥታ ከማስከበር ባሻገር ለትውልድ የሚሻገር አሻራችንን በማኖር ታሪክ እየተጋራን ነው

አዳማ ፤ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ ሰላምና ፀጥታ ከማስከበር ባሻገር ለትውልድ የሚሻገር አሻራችንን በማኖር ታሪክ እየተጋራን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ገለጹ።

የፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖችና አባላት በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳታፊ በመሆን በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር አሻራቸውን አኑረዋል።

ከመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች መካከል ኢንስፔክተር አህመድ ሁሴን፤ በሙያቸው የሀገርንና የህዝብን ተልእኮ በብቃት ከመወጣት በተጓዳኝ በልማት ስራዎች ላይ መሳተፍ አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በዛሬው እለት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ለትውልድ የሚሻገር አሻራቸውን ማኖራቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት በተሰማሩባቸው ሀገራዊ ተልእኮዎች ሁሉ ሃላፊነታቸውን በላቀ ብቃት እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።

ከፖሊሳዊ ተልዕኳችን ጎን ለጎን በማህበረሰብ አገልግሎትና በሀገር ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ላይ የሚኖረን ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሌላኛው የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ ረዳት ኢንስፔክተር ሮባ ሞቱቡሌ፤ የፖሊስ አባላቱ በተሰማሩባቸው ሀገራዊ ተልእኮዎች ሁሉ ሃላፊነታቸውን በላቀ ብቃት እየተወጡ መሆኑን ገልጸው በልማት ስራዎችም የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በዛሬው እለትም ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን አሻራችንን በማኖራችን ላቅ ያለ ክብርና ደስታ ይሰማናል ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም