ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ በተወጠነው አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መሳተፍ ዕድለኝነት ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ በተወጠነው አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መሳተፍ ዕድለኝነት ነው
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መሳተፍ ዕድለኝነት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አመራር አባላትና ሰራተኞች ገለጹ።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አመራር አባላትና፣ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዬን ኝግኝ ተከላ መርሃ ግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የ2018 ዓ ም አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርን ሰኔ 8 በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሲዲ ሀይቅ ዳርቻ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
በክረምትና በበጋ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉም ይፋ ያደረጉ ሲሆን ለግቡ ስኬት ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በዛሬው ዕለትም በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ በመውጣት አረንጓዴ ዐሻራውን እያኖረ ይገኛል።
በዚህም የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አመራር አባላትና ሰራተኞችም በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አረንጓዴ ዐሻራቸውን በማኖር የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ሀገር አቀፍ ንቅናቄን ተቀላቅለዋል።
የኢኒስቲትዩቱ ሰራተኞች በዛሬው ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለምግብነት የሚያገለግሉ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።
በኢኒስቲትዩቱ የዳታ ሴንተር መሰረተ ልማት ዳይሬክተር ደረጀ ደገፋ ለኢዜአ በሰጡት፤ አስተያየት አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከጅምሩ አንስቶ በከፍተኛ ተነሳሽነት ጉጉት እየተሳተፉ መሆን ተናግረዋል።
መርሃ ግብሩ የአየር ንብረት ለውጥን በማስተካከል ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ዓይተኛ ሚና እንዳለው አንስተው፤በዚህ መርሃ ግብር በመሳተፌ ዕደለኛ ነኝ ብለዋል።
ችግኝ መትከል ብቻውን ግብ አይየደለም ያሉት አቶ ደረጀ መንከባብና ለውጤት ማብቃት የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የኢኒስቲትዩቱ ዳታ ሴንተር መሰረተ ልማት ምትክል ዳይሬክተር በድሉ ከበደ በበኩላቸው፤ተስፋን ለነገ ትውልድ ማድረስ አሁን ያለው ትውልድ አደራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በመሆንም በአረንጓዴ ዐሻራ ላይ መሳተፍ ብሎም ውጤታማ እንዲሆን የማድረግ ታሪካዊ ግዴታ አለብን ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ፤ እኔም ቀጣይነት ባለው መልኩ በአረንጓዴ ዐሻራ በመሳተፍ የበኩሌን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
በኢኒስቲትዩቱ የሳይበር ዲቪዠን ውስጥ በባለሙያነት እያገለገለች የምትገኘው ወጣት በአርያም ተመስገን በበኩሏ፤በአረንጓዴ አሻራ ለመጀመሪያ ጊዜ መሳተፏን ገልጻለች።
በአረንጓዴ ዐሻራ ከዚህ ቀደም አለመሳተፌ ይቆጨኝ ነበር ያለችው ወጣት በአርያም ዛሬ በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በመሳተፍ ህልሜን አሳክቻለሁ ስትልም አክላለች።
ሌላዋ የኢኒስቲትዩቱ የሰራተኛ ወይዘሮ ኤልሳቤት ተስፋዬ ከልጄ ጋር በመሆን አረንጓዴ ዐሻራዬን አኑሬያለው፤ በዚህ ደግሞ ልዩ ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ ገልጸዋል።