ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች አና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች አና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018  ዓ.ም  አረንጓዴ  ዐሻራ መርሃ ግብርን ሰኔ 8 በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሲዲ ሀይቅ ዳርቻ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።  

በክረምትና በበጋ በአጠቃላይ ስምንት ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉም ይፋ ያደረጉ ሲሆን ለግቡ ስኬት ኢትዮጵያውያን ርብርብ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።  

በዛሬው ዕለትም በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ በመውጣት አረንጓዴ አሻራውን እያኖረ ይገኛል። 

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ሀገር አቀፍ ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል። 

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በዛሬው ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለምግብነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ችግኞችን ተክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም