ቀጥታ፡

 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያሳደገ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

አሶሳ ፤ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር  የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በአቡራሞ ወረዳ  አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ከማስገኘቱ ባለፈ የኢትዮጵያዊያን መገለጫ ሆኗል።


 

መርሃግብሩ የደን ሽፋንን በማሳደግ የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በክልሉ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ በማድረግ የግድቡን ዘላቂ ደህንነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር ህብረተሰቡ በንቃት  እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም