የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት - ኢዜአ አማርኛ
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
ሀገራዊ ራዕያችንን ለማሳካትና ዘላቂነት ያለው መጻኢ ዕድል ለመፍጠር ወጣት ኃይላችንን በዕውቀት፣ በፈጠራና በአመራር ብቃት እየገነባን ነው።
ዛሬ "አረንጓዴ አሻራ ለዘለቄታዊ የግብርና ልማትና አረንጓዴ ኢኖቬሽን" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን 6ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአመራር ኮንፈረንስና የዲፕሎማሲ ጉባኤ አስጀምረናል፡፡
የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማሳካት፣ ሁሉንም አሳታፊ የሆነ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ተግተን በመነሳት፤ የሀገሪቱን የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና ዘርፍ የማዘመን፣ የምግብ ዋስትናንና ብሔራዊ ክብርን የማረጋገጥ ሥራዎችን እያከናወንን እንገኛለን፡፡
ይህንን ሀገራዊ ራዕይ ይበልጥ ለማሳካት ዋነኛ አቅማችን የሆነውን ወጣት ኃይላችንን በዕውቀት፣ በፈጠራና በአመራር ብቃት እንዲገነባ እያደረግን ነው፡፡
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ኮንፈረንስ ወጣት መሪዎቻችን በምግብ ሉዓላዊነት፣ በአየር ንብረት መቋቋም እና በታዳሽ ኃይል ዙሪያ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችንና አጋርነቶችን የሚፈጥሩበት፣ እንዲሁም ለነገው ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ራሳቸውን በተግባር የሚያዘጋጁበት ነው፡፡
ዛሬ በወጣቶቻችን ላይ የምናደርገው እያንዳንዱ ኢንቨስትመንት፣ ለምንገነባት የበለጸገች ሀገር ሁነኛ ዓምድ ነው።
አረንጓዴ ዐሻራን እያኖርን የትውልዱን የለመለመ ተስፋ እየተከልን፣ አረንጓዴና ዘላቂ የሀገር ግንባታን ለማፋጠን እንትጋ።