በሐረሪ ክልል በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዝግጅት ተጠናቋል - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዝግጅት ተጠናቋል
ሐረር፤ሐምሌ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በሐረሪ ክልል በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው ሀገራዊ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ዑመር ተናገሩ።
የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ዑመር የመርሃ ግብሩን ዝግጅት አስመልክተው ለኢዜአ እንዳሉት፤ በክልሉ ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሲደረግ የነበረው ዝግጅት ተጠናቋል።
በክልሉ በሚከናወነው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የታቀደውን ለማሳካት ዝግጅት መደረጉንም አክለዋል።
በክልሉ በተለያዩ 14 ቦታዎች ላይ በአንድ ጀንበር ችግኝ ለመትከል የጉድጓድ ቁፋሮና የማጓጓዝ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በክልሉ ከተማና ገጠር ወረዳዎች ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ግንዛቤ የመስጠት ሥራ መጠናቀቁንም ተናግረዋል።
በዚህ መርሃ ግብር የክልሉ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የመከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ አመራርና አባላት እንዲሁም የክልሉ የጸጥታ ኃይል አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።
በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉም ጠቁመዋል።