ቀጥታ፡

የስልታዊ ቡድን ምክክር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 250 አባላት ባሉት 16 ስልታዊ ቡድኖች የተደራጁ ተመካካሪዎች ምክክር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በ250 አባላት የተደራጁ 16 ስልታዊ ቡድኖች ከጥቃቅንና ንዑስ ቡድኖች በተገኙና በተጠናቀሩ የአጀንዳ ምክረሃሳቦች ላይ ከትላንት ጀምረው ተመካክረዋል፡፡

ትላንት በነበረው የምክክር ውሎ ከእያንዳንዱ ሰልታዊ ቡድን በተመረጡ 25 የአጀንዳ ምክረሃሳብ አጠናካሪዎች አማካኝነነት የተጠናቀሩ ምክረሃሳቦችን ያዳመጠው 16ቱ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድን አባላት፣ በጥቃቅንና በንዑስ ቡድኖች ተነስተው በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ያልተካተቱ፣ በአግባቡ ያልተብራሩ ያላቸውን ሃሳቦች ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡

ስልታዊ ቡድኖቹ በዛሬው ውሏቸው የተሰጡ አስተያየቶች ተካተውበት በድጋሚ የተደራጀውን ቃለ ጉባኤ የጋራ በማድረግ በቀጣይ ለሚደረገው እና 500 ተመካካሪዎችን ለያዙ ስምንት ቡድኖች ምክክር ዝግጅት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡


 

ነገው በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ እገዛ የሚያደርጉ የክልል (ከተማ መስተዳድር) እና የፌዴራል ተወካዮች ምርጫ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 250 አባላት ባሉት 16 ስልታዊ ቡድኖች የተደራጁ ተመካካሪዎች ምክክር ዛሬ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡

በ250 አባላት የተደራጁ 16 ስልታዊ ቡድኖች ከጥቃቅንና ንዑስ ቡድኖች በተገኙና በተጠናቀሩ የአጀንዳ ምክረሃሳቦች ላይ ከትላንት ሐምሌ 22/2018 ኣ.ም ጀምረው ተመካክረዋል፡፡

ትላንት ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም በነበረው የምክክር ውሎ ከእያንዳንዱ ሰልታዊ ቡድን በተመረጡ 25 የአጀንዳ ምክረሃሳብ አጠናካሪዎች አማካኝነነት የተጠናቀሩ ምክረሃሳቦችን ያዳመጠው 16ቱ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድን አባላት፣ በጥቃቅንና በንዑስ ቡድኖች ተነስተው በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ያልተካተቱ፣ በአግባቡ ያልተብራሩ ያላቸውን ሃሳቦች ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡


 

ስልታዊ ቡድኖቹ በዛሬው ውሏቸው የተሰጡ አስተያየቶች ተካተውበት በድጋሜ የተደራጀውን ቃለ ጉባኤ የጋራ በማድረግ በቀጣይ ለሚደረገው እና 500 ተመካካሪዎችን ለያዙ 8 ቡድኖች ምክክር ዝግጅት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡

በነገው ዕለት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ እገዛ የሚያደርጉ የክልል (ከተማ መስተዳደር) እና የፌዴራል ተወካዮች ምርጫ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም