በዋናው የምክክር ጉባኤ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት የተሻለች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ገንቢ ምክክር እያካሄድን ነው - ኢዜአ አማርኛ
በዋናው የምክክር ጉባኤ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት የተሻለች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ገንቢ ምክክር እያካሄድን ነው
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ በዋናው የምክክር ጉባኤ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት የተሻለች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ገንቢ ምክክር እያካሄዱ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዋናው የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
በጉባኤው በኮሚሽኑ በተለዩ የሀገር ግንባታ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የውክልናና የምርጫ ሥርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች እና የተቋማት ግንባታ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ተመካካሪዎች እየመከሩ ይገኛሉ።
በተጨማሪም በሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ በአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ዕጣ ፈንታ፣ በሙስና፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ በተለዩ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎችና በተለያዩ ንዑስ ሐሳቦች ላይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎችን ጨምሮ ከአራቱም ማዕዘናት የተውጣጡ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት እየተመካከሩ ይገኛሉ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲ ተወካይ ጣሂር መሐመድ እና የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ገነነ ገረቡ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የምክክር ጉባኤው ለኢትዮጵያ አዲስ የምክክር ባህል የከፈተ ነው።
በምክክር ጉባኤው የግልና የቡድን ፍላጎቶችን በማጥበብና ሀገርን በማስቀደም በተመካካሪዎች መካከል በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ ሰላማዊና አሳታፊ ምክክር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
በዋናው የምክክር ጉባኤ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት የተሻለች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ገንቢ ምክክር እያካሄዱ መሆኑን አንስተዋል።
በዋናው የምክክር ጉባኤ በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በማጎልበት የተሻለች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ገንቢ ምክክር እያካሄዱ መሆኑንም አክለዋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ተወካይና ተመካካሪ ጣሂር መሐመድ እንዳሉት፤ በምክክር ጉባኤው ሀገርን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ምክክር እየተደረገ ነው።
በዋናው የምክክር ጉባኤ የሚመከርባቸው ዐበይትና ንዑሳን አጀንዳዎችም በተመካካሪዎች መካከል በነፃነትና በአካታችነት እየተመከረባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የምክክር ጉባኤው የኢትዮጵያን መሠረታዊና መዋቅራዊ ችግሮች በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ መግባባት በመፍጠር መፍትሔ የሚሰጥ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተናግረዋል።
ለሕዝብ ጥያቄዎች ዘላቂ ምላሽ ለመስጠትና መግባባት ለመፍጠርም ወሳኝ ዕድል መሆኑን አንስተዋል።
የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንትና ተመካካሪ ገነነ ገረቡ በበኩላቸው፤ በምክክር ጉባኤው አንዱ የሌላውን ሃሳብ መረዳት በሚያስችል መልኩ ማንኛውም የሕዝብ አጀንዳ በነፃነት እየተንጸባረቀ ነው ብለዋል።
የምክክር ጉባኤው ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶች ለቀጣዩ ትውልድ እንዳይተላለፉ ለማድረግ ስልጡን ምክክር እያደረግን ነው ብለዋል።
በተመካካሪዎች መካከልም በአርአያነት የሚወሰድ ነፃ ምክክር እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።