ቀጥታ፡

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።

"ሁሉ አቀፍ እመርታ ፣ ለሁለንተናዊ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የከፍተኛ አመራሮች የዉይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።


 

ርዕስ መስተዳድሩ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር  በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲና በመንግሥት ስራዎች አፈፃፀም ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።

በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች መከናወናቸውን  ተናግረዋል።

የህዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ክልሉን የህብረ ብሄራዊነት ተምሳሌት ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል።

በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከርና የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ የመድረኩ ዋና ዓላማ ስለመሆኑም ገልጸዋል። 

በመድረኩ የክልሉ  ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ዕህፈት ቤት ሀላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ጨምሮ የክልል ፣ የዞን ፣ የልዩ ወረዳ ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም