ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያ የሚበጅና አዋጭ መንገድ ነው - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ - ኢዜአ አማርኛ
ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያ የሚበጅና አዋጭ መንገድ ነው - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ በውይይትና መግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሔ የማምጣት አዋጭ መንገድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ።
ዋና ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሂደትን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች በስምንቱ አጀንዳዎች ላይ በተለያዩ ቡድኖች ሆነው ውይይት ማድረግ መቀጠላቸውን ገልጸዋል።
ተመካካሪዎች በመከባበርና በመደማመጥ በነጻነት ሀሳባቸውን እያንሸራሸሩ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
በምክክሩ የተለያዩ ሀሳቦች መነሳታቸውና በጥልቀት መዳሰሳቸው በቀጣዩ ሀሳቦችን ወደ አንድ የመሰብሰብ ምዕራፍ ሂደት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።
የምክክር ጉባኤው የመጨረሻ ምዕራፍ የጋራ መግባባት እንደሆነ ጠቅሰው ለዚህም መሳካት አሁን እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች ወሳኝ አበርክቶ አላቸው ነው ያሉት።
አጠቃላይ እስከ አሁን በጉባኤው ላይ የታዩ ነገሮች በጣም አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ።
ዋና ኮሚሽነሩ ለኢትዮጵያ የምክክር ሂደቱ አዋጭና ዘላቂ መፍትሄን መምጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።