ቀጥታ፡

የሆለታ ወታደራዊ አካዳሚ 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ሆለታ በሚገኘው የአካዳሚው ግቢ ያሰለጠናቸውን 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ-ሰርዓቱ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄነራል ይመር መኮንን፣ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው ሀብታሙ፣ የክብር ጄነራል መኮንኖች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።


 

በመርሃግብሩ በስልጠናው ብልጫ ያመጡ ዕጩ መኮንኖች በጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የማዕረግ ማልበስ ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ጌታቸው ሀብታሙ፤ ተመራቂዎቹ የወሰዱት ስልጠና ሁለንተናዊ የአመራር ጥንካሬን የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል።


 

ዕጩ መኮንኖቹ ከትምህርትና ስልጠናው ያገኙት እውቀት እና ክህሎት ማንኛውምንም የሠራዊት የግዳጅ ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አቅም አጎናፅፏቸዋል ብለዋል።

ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አፍሪካውያን ዕጩ መኮንኖችም ስልጠናቸውን አጠናቀው መመረቃቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም