ቀጥታ፡

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለችና የጸናች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018(ኢዜአ)፦ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለችና የጸናች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እና አራት ሺህ የሕዝብ ተወካይ ተመካካሪዎች በተገኙበት ዋናው የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 8 ቀን 2018 . በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መጀመሩ ይታወቃል።


 

ከሐምሌ 13 ቀን 2018 . ጀምሮም የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮችና በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን የሚወክሉ ተመካካሪዎች በንዑስ ቡድኖች ተከፋፍለው በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ እየተመካከሩ ይገኛሉ።

ተመካካሪ ተስፋዬ አየለ እንድገለጹት፤ የምክክር ሂደቱ የጸናች ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ሁነኛ መንገድ በመሆኑ እየመከሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የምክክር ጉባኤው ሁሉንም ያካተተ፣ ያሳተፈ እና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥር ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስተላለፍ እየመከሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡


 

ሊቀ-ካህናት ጌታሰው በላይ በበኩላቸው፤ በምክክሩ የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች እና ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች በመመካከር ላይ መሆናቸውን አንስተዋል።

ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተፈጠረው ታላቅ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው የበለጸገች ሀገርን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ዕድል በአግባቡ በመጠቀምና አንዱ የአንዱን ሃሳብ በመረዳት ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስተላለፍ እየመከርን ነው ብለዋል።


 

በምክክሩ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሀገርን መጻኢ ዕድል ብሩህ ለማድረግ እየመከሩ መሆናቸውንም የገለጸው ደግሞ ወጣት  ቸሩ በየነ ነው።

የምክክር ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ተደራጅቶ መጀመሩንና አሁንም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልጾ ሁሉንም ያካተተ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋና ብሩህ መደላድል ይዞ እንደሚመጣ እምነቱን ተናግሯል፡፡   


 

ሌላኛው አስተያያት ሰጪ ማርቆስ ገዛኸኝ ምክክሩ ትስስርን የሚያጠናክር፤ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ እንዲሁም መጻኢ ዕድልን የሚወስን በመሆኑ በንቃት አየተሳተፋ መሆኑን ገልጸዋል።

ምክክሩ ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚቆሙበትን የአንድነት ምዕራፍ ለመፍጠር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አመልክተው ሂደቱ ለጠንካራ የሀገር ግንባታ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም