ቀጥታ፡

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ዐበይት መረጃዎች

በትናንትው ዕለት በሚመካከሩበት የአጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በባለሙያዎች ቡድን (Panel of Experts) የተለያዩ የምክክር ግብዓቶችን የሚሰጡ ገለፃዎች የተደረገላቸው ተመካካሪዎች ዛሬ በ50 ቡድን በመሆን ምክክሩን ቀጥለዋል፡፡

ተመካካሪዎች በቀደሙት ቀናት በአስር አስር የቡድን አባላት በተወያዩባቸው ንዑሳን አጀንዳዎች ላይ ያነሷቸውን ሃሳቦች በቃለ-ጉባኤ አስፈረው በሃምሳ ለተደራጀው ቡድናቸው አቅርበዋል።


 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሚሽኑ ለአካታችነት እና ለልዩ ፍላጎቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአካል ጉዳተኛ ተመካካሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም