በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምግብ ሉዓላዊነትንና የኢንዱስትሪ ግብአትን መሰረት ያደረጉ የግብርና ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምግብ ሉዓላዊነትንና የኢንዱስትሪ ግብአትን መሰረት ያደረጉ የግብርና ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው
አርባ ምንጭ፤ ሐምሌ 17/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምግብ ሉዓላዊነትንና የኢንዱስትሪ ግብአትን መሰረት ያደረጉ የግብርና ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ውጤትም እየተመዘገበ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉን መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ኢንሼቲቮች እየተተገበሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በሌማት ትሩፋት፣ በስንዴ ልማት እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከተፈጥሮ ሃብት ልማት ባለፈ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ሂደት የተመዘገበውን ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል።
በመሆኑም የምግብ ሉዓላዊነትንና የኢንዱስትሪ ግብአትን መሰረት ያደረጉ የግብርና ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ውጤትም እየተመዘገበባቸው ይገኛል ብለዋል።
በቱሪዝም እና የማዕድን ሃብት ልማት፣ መስኖ ልማትና በኩታ ገጠም እርሻ፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት አስደናቂ ስኬት መመዝገቡን ጠቅሰዋል።