ምክር ቤቱ የህዝቡ የልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ውጤታማ የክትትልና የቁጥጥር ስራ አከናውኗል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የህዝቡ የልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ውጤታማ የክትትልና የቁጥጥር ስራ አከናውኗል
አርባምንጭ፤ ሐምሌ 17/2018 (ኢዜአ)፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህዝቡ የልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ውጤታማ የክትትልና የቁጥጥር ስራ ማከናወኑን ገለጸ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወላይቴ ቢቶ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ አካላትን የስራ እንቅስቃሴ በመከታተልና በመቆጣጠር ውጤታማ ተግባር አከናውኗል።
የአስፈጻሚ አካላት የልማት እንቅስቃሴን በቋሚ ኮሚቴዎች በማስገምገምና በመስክ ስራ ክትትልና ድጋፍ ጠንካራ ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል።
በበጀት ዓመቱ በክልሉ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ፣ የህዝቡን የልማት ፍላጎት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አንስተዋል ።
በተለይም የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንዲመለሱ የተደረገ ጥረት ውጤታማ መሆኑን አመልክተዋል።