ቀጥታ፡

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የእንጦጦ - ቀበናን የወንዝ እና የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ ዋናው ማዕከል እና የክልል ቅ/ፅህፈት ቤት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በመዲናዋ በመፍጠር እና በመፍጠን የተገነቡ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክቶችን ተዟዙረዉ ጎብኝተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋናው ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና ሌሎችም የፌዴራል፣ የአዲስ አበባ እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።


 

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የብልፅግና ፓርቲ ምናብ ወደ ውጤት እየተቀየረባት የምትገኘው ውቧ መዲናችን ሁሌም አዲስ እየሆነች ትገኘለች  ብለዋል።

አዲስ አበባ የብልፅግና አይቀሬነት ማሳያ መሆኗን የገለፁት ከንቲባ አዳነች ተግተን በመሥራት በላቁ አዳዲስ ድሎች እንገናኛለን ብለዋል።


 

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው፤ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች የከተማዋን  ገፅታ ከመገንባታቸው ባሻገር የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ከፍ ማድረጋቸውን አስረድተዋል።


 

ከፍተኛ አመራሮች 10.5 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ ሱቆች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ቤተ መፅሀፍት ፣ የከተማዋ ነዋሪ አንዱ የመዝናኛ ማዕከል የሆነውን የቀበና ግድብ እና ሌሎችም የህዝብ መገልገያዎች ያሉትን የእንጦጦ - ቀበና የወንዝ ዳር ፕሮጀክትን ተዟዙረዉ መጎብኘታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም