ቀጥታ፡

የገበያ አማራጮችን በማስፋትና ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር ለገበያ መረጋጋት የሚደረገው የተቀናጀ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል

ኮምቦልቻ ፤ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፡-  የገበያ አማራጮችን በማስፋት፣ የምርት አቅርቦትን በማሳለጥና ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር ለገበያ መረጋጋት የሚደረገው የተቀናጀ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የተጠናቀቀው በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የአዲሱን በጀት ዓመት እቅድ የትውውቅ መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እያካሄደ ነው።


 

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም መሐመድ (ዶ/ር)፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገበያ አቅርቦትና ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ብዙ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም የገበያ አማራጮችን በማስፋት፣ የምርት አቅርቦትን በማሳለጥና ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር ለገበያ መረጋጋት የሚደረገው የተቀናጀ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


 

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ንግድንና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ መላኩ፤ በከተማው የገበያ ማዕከላትን  በማስፋፋት የምርት አቅርቦትና ተደራሽነት ላይ በቅንጅት መሰራቱን አንስተው ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑን አረጋግጠዋል።

በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የወረዳዎች በየደረጃው ያሉ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም