ብልጽግና ፓርቲ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል-አቶ አደም ፋራህ - ኢዜአ አማርኛ
ብልጽግና ፓርቲ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል-አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ወደ ተግባር በማስገባት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።
በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የፓርቲው የዋናው ጽህፈት ቤት እና የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮች ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የተቋማት ግንባታ ስራ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የተከናወኑ የተለያዩ ስራዎች ስኬት አስመዝግበዋል።
የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተከናውነው በርካታ ስኬት መምጣቱን አንስተው፤ የተመዘገበውን ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል የፓርቲው ቀጣይ ትኩረት መሆኑንም አብራርተዋል።
አመራሮቹ ከጉብኝት ባለፈ በመዲናዋ ባሉ የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ችግኝ በመትከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።