ቀጥታ፡

የመደመር እይታ

ሀገራዊ ምክክር እንደ ዘላቂ መፍትሔ

በሀገራችን የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፣ በውይይትና በምክክር ጎልብተው፣ አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት መድረክ ነው። ሁሉም ስለ ሀገር የሚያገባው አካል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ አዋጥቶና ተነጋግሮ መግባባት የሚፈጥርበት ምኅዳር ነው። በውይይትና በምክክር ወደ መግባባት የሚደረስበት መንገድ ነው።

በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ከገጠሙን እጥረቶች አንዱ ሀገራዊ ምክክር ነው። በሀገረ መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ተመካክሮ፣ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ፣ የተግባባባቸውን በሕግና በሥርዓት አጽንቶ፣ ያልተግባባባቸውን ደግሞ ለወደፊት ምክክሮች አቆይቶ አልተጓዘም።በዚህ የተነሣ በየጊዜው ቅሬታ፣ ኩርፊያ፣ አብዮት፣ዐመጽ ይፈጠራል። ነገሮች በተጠናጠል እየቀረቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል። ሁለንተናዊ ዕይታ ይጠፋል። ሀገራዊ ምክክር ይሄን የዘመናት ስብራት የሚጠግን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም