ቀጥታ፡

ጨፌ ኦሮሚያ 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ ጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን  በአዳማ ገልመ ጨፌ ማካሄድ ጀምሯል። 

ጉባኤው የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ በጥልቀት በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሏል።


 

በተጨማሪም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ኦዲት መስሪያ ቤት ሪፖርቶችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል። 

እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እቅድ ማስፈጸሚያ በጀትን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት መክሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም