ቀጥታ፡

የኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑ አገልግሎት የሚደነቅ ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 11/2018 (ኢዜአ) ፦የኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑ በፍቅር የምትሰጡት እጅግ የላቀ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከልብ የሚደነቅ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።


 

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ለ5ኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ700 በላይ የልብ ህሙማንን በማከም ከስቃይ ያዳኑት Heart Attack Ethiopia (የኸርት አታክ ኢትዮጵያ) ፋውንዴሽን መስራቾችን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑን በጽህፈት ቤታቸው መቀበላቸውን ገልጸዋል።

የኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑ በፍቅር የምትሰጡት እጅግ የላቀ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከልብ የሚደነቅ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በቀጣይም የህክምና ተራ እየጠበቁ ላሉ የልብ ህሙማን ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ በጋራ ተቀናጅተን የብዙዎችን ሕይወት ለመታደግ አብረን ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል።


 

እንደዚህ ትልቅ የህክምና ቡድን አቀናጅታችሁ ለወገኖቻችሁ ትልቅ ህይወትን የማዳን ስራ ለመተግበር የተጋችሁ መስራቾቹን እና የበጎ ፍቃድ የህክምና ቡድኑን አባላት በራሴ እና በታካሚዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም