ቀጥታ፡

በሀገራዊ ምክክሩ ማንኛውም ወገን በፍትሐዊነት በጋራ መግባባት ላይ እንዲደርስ የሚያስችል መድረክ ተፈጥሯል - ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2018(ኢዜአ)፦ በሀገራዊ ምክክሩ ማንኛውም ወገን በፍትሐዊነት በጋራ መግባባት ላይ እንዲደርስ የሚያስችል መድረክ ተፈጥሯል ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።

ሀገራዊ ምክክር እንደተለመደው የፖለቲካ ክርክር በአብላጫ ድምፅ የሚወሰን ሂደት ሳይሆን፣ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ታሪካዊ መድረክ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በሀገራዊ ምክክሩ ማንኛውም ወገን በፍትሐዊነት በጋራ መግባባት ላይ እንዲደርስ የሚያስችል መድረክ ተፈጥሯል ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ታሪካዊ መድረክ ነው ሲሉም አክለዋል።

ከመክፈቻው ቀን ጀምሮ በምክክር ሂደቱ ላይ ለተሰማሩ አራት ሺህ ተሳታፊዎች ስለ ምክክሩ መርሆዎችና የውሳኔ አሰጣጥ ስነ ዘዴዎች ላይ ሰፊ ገለጻ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል ነው ያሉት።

ሀገራዊ ምክክሩ የጋራ እጣ ፈንታን ለመወሰን የሚደረግ እንጂ፣ አሸናፊና ተሸናፊን ለመለየት የሚደረግ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

የምክክር ሂደቱ ኢትዮጵያውያን በጋራ መግባባት ለነገዋ የተሻለች ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥሉበት መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም