የክልሉን እምቅ አቅሞች በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል- ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን - ኢዜአ አማርኛ
የክልሉን እምቅ አቅሞች በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል- ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
አሶሳ ፤ሀምሌ 11/2018 (ኢዜአ)፡- በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የክልሉን እምቅ ሃብቶች በማልማት በሁሉም ዘርፎች የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ ክልሉ በብዙ መልኩ መልማት የሚችል እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ በዚሁ መሰረት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለይም በማዕድን፣ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጅታላይዜሽን እና ሌሎችም ሴክተሮች እመርታዊ እድገትና ማንሰራራት የታየባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም በማዕድን ሃብት ልማትና ተጠቃሚነት ረገድ መሰረታዊ የሚባል ለውጥና ስኬት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተደመረ አቅም የክልሉን እምቅ አቅሞች በማልማት በሁሉም ዘርፎች የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች በክልሉ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ተናግረዋል።