ቀጥታ፡

ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው - አቶ ጌታቸው ረዳ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2018(ኢዜአ)፦ ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው ሲሉ የስምረት ፓርቲ ሊቀ መንበር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ህዘብ ላይ የሚፈፅመውን አፈናና ጭቆና የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ህገ-ወጡ የህወሓት ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርግ በተደራጀ መልኩ ልንታገለውና ድምፃችንን ልናሰማ ይገባል።


 

ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ወጣቶችን ወደ ሱዳን መሸጥ ያቁም ያሉ ሲሆን ህገ ወጥ ቡድኑ የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ እያስቀረ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አሁን ላይ የፕሪቶርያው ስምምነት ለትግራይ ህዝብ ያመጣው እፎይታ መገታቱን አስታውሰው የተገኘውን ለውጥ በመቀልበስ የጊዜያዊ አስተዳደሩን በመንፈቅለ መንግስት ማውረዱና ራሱ መሾሙን አንስተዋል።

ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን በዚህ ሳያበቃ ወጣቶችን በግዳጅ ለውትድርና እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።


 

ህገ-ወጡ የህወሓት ቡድን እናቶች ልጆቻቸው ከእቅፋቸው በመንጠቅ ወደ ጦር ካምፕ በማስገባትና እናቶች በማሰር ኢሰብአዊ ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል ነው ያሉት።

ሕገ ወጡ ህወሃት ለስልጣንና ለሀብት ብቻ ትኩረት በማድረግ ወጣቶችን ለስቃይ እየዳረገ እንደሚገኝ ገልፀው ቡድኑ እያስከተለ ያለውን ጥፋት በቃህ ሊባል እንደሚገባውም አመልክተዋል።

ቡድኑ ወጣቶችን ያለፈቃዳቸው እያፈሰ ወደ ጦር ካምፕ ከማስገባት በተጨማሪ ለሱዳንና ለኤርትራ እየሸጠ እንደሚገኝ ገልፀው ይህም ለሰብዓዊ መብት የማይጨነቅ አምባገነን መሆኑን የሚሳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም