ቀጥታ፡

ከጋምቤላ ክልል ጋር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በሌሎች ሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ በትብብር እንሰራለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 10/ 2018 (ኢዜአ)፦ ከጋምቤላ ክልል ጋር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በሌሎች ሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ በትብብር እንሰራለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

በዚህም ወቅት በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ፣ በኮሪደር ልማት፣ እንዲሁም በሌሎች የሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ እርስ በርስ ልምድ እየተለዋወጥን፣ትብብራችንን አጠናክረን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም