ቀጥታ፡

በሀረሪ ክልል በበጎ ፈቃድ ተግባራት 246 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ተደርገዋል - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2018(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል በ2018 የበጀት ዓመት በበጎ ፈቃድ ተግባራት ከ246 ሺህ የሚበልጡ ዜጎች ተጠቃሚ መደረጋቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ተኛ ዙር 5ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት በበጎ ፈቃድ እና የህብረተሰብ አገልግሎት ስራዎች 66 ሺ 594 በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ197 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ግምት ያለው አገልግሎት እንደተሰጠም ተናግረዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 246 ሺ 367 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስና በመገንባት፣በደም ልገሳ፣ ለተማሪዎች ድጋፍ በማድረግና በመሳሰሉት ተሳትፎዎች ውጤተማ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም