አገልግሎቱ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
አገልግሎቱ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 9 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት፣ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን እና ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድጉ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፤ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፥ተቋሙ ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት፣ የአሰራር ሥርዓቱን በማዘመን እና ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ የሚያሳድጉ ተጨባጭ ለውጦች ማምጣቱን ገልጸዋል።
የፓስፖርት እና የቪዛ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የይለፍ ሰነዶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፈው በጥራት እና በደህንነት እንዲመረት ተደርጓል ብለዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርቶች ታትመው ለዜጎች መሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት መስጫ ማዕከላት ከነበሩበት 12 ወደ 23 በማሳደግ ተደራሽነቱ ማስፋፋት መቻሉን ጠቅሰው፥ በአየር እና በየብስ የድንበር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ከ7 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ መንገደኞች ቀልጣፋ አገልግሎት መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡
የተቋሙን የሰው ኃይል አደረጃጀት እና ልማት በማሻሻል አገልግሎቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ለውጡን ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደነበሩም ገልጸዋል።